Samling 2
ወጎች ባህሎች ፣ ለልጆቻችን ማስተላለፍ የምንፈልገው የትኛውን ወጋችን ወይም ባህላችንን ነው?
የዚህ ስብሰባ ዓላማ እንዴት አንዳንድ ባህሎች ወይም ወጎች የጎሳ ማንነትን ሲደግፉና ሲያጠናክሩ አንዳድ ባህሎች ወይም ወጎች ደግሞ ጎጂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለተከፍዮቹ የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው።. ልላ ተጨማሪ ግቡ ደግሞ ባህል ወይም ወግ ምንነቱንና እነዴትም እንደሚለወጥና እንደሁም ወደሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍን በሚመለከት ስላላችው የመምረጥ እድሎች የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ነው። ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ባህሎች ወይም ወጎች የሚሰጡት ክበር የላቀ እንዲሆን ማድረግ ደግሞ ሌላኛው ግብ ነው።